Directorate

AMCE:-ስልጠናዎችን የኪስ መደጎሚያ አማራጮች አድረጎ የማየት ዝንባሌ እስካላቆመ ድረስ የምናሰበው ለውጥ ይዘገይብናል !!! አቶ አያሌው አበራ የአርባምንጭ ትምህርት ኮሌጅ ዋና ዲን!!!

!

AMCE:-ስልጠናዎችን የኪስ መደጎሚያ አማራጮች አድረጎ የማየት ዝንባሌ እስካላቆመ ድረስ የምናሰበው ለውጥ ይዘገይብናል !!! አቶ አያሌው አበራ የአርባምንጭ ትምህርት ኮሌጅ ዋና ዲን!!!!
————————————-
ከሰሞኑ በአርባምንጭ ትምህርት ኮሌጅ የተለየዩ የሥልጠና መርሀግብሮች ተከናውነዋል ። በመረሃግብሮቹ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ አያሌው አበራ ስልጠናዎች የዕውቀትና የክሎት ሽግግር ለመፍጠር የሚያግዙ መሣሪያዎች እንጂ የግል ጥቅም መደጎሚያ አማራጭ ገቢ ተደረገው መታሰብ የለባቸውም ብለዋል ።
ተቋሙ ያራስ አቅምን ከማስተባበር ጀምሮ ከአጋር ተቋማት ጋር በመቀናጀት የተለያዩ ሥልጠናዎችን በየደረጃው ለሉ ሠራተኞች በቀጣይነት ይሰጣል ያሉት ዋና ዲኑ ሠልጠኞች ተገቢውን እውቀትና ክህሎት በመቀሰም ተቋማዊ የሪፎርም ስራን እንዲያግዙ ጥሪ አቅረበዋል ።
ባሳለፍነው ሳምንታት ከተካሄዱት የሥልጠና መረሀግብሮች በኮሌጁ የሁል ጊዜ አጋር በ ECDD(Ethiopian Center For Disability And Development )አማካኝነት Training on disability Inclusive awareness በሚል ርዕሰ ለኮሌጁ መምህራን የተሠጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን በኮሌጁ የማህበረሰብ አገልግሎት አስተባባሪነት በአርባምንጭ ከተማ ለሚገኙ ለቅደመ መደበኛ መምህራን የተሰጠው የክህሎት ሽግግር ስልጠና በሁለተኛው የሥልጠና መረሀ ግብር ተከናውኗል ።
ስልጠናውን በሚመለከት ከኮሌጁ ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ጋር አጭር ቆይታ ያደረጉት በኮሌጁ የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ፋሲል ግርማ እና የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተሩ አቶ መዝገበ መና ሲሆኑ ሀላፊዎች በቆይታቸው ሀሳባቸውን አጋርተውናል ።
አቶ ፋሲል የልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች በዘመናት ውስጥ ተረስተውና ተዘንግተው ተገቢው ትኩረት ሳይሰጣቸው ከመቆየታቸውም በላይ የተለያዩ ስያሜ እየተሰጣቸው ከማህበረሰቡ ሲገለሉና ሲለዩ ይኖሩ እንደነበረ ገልፀው ፤ ዛሬ ላይም ቢሆን የተወሰኑ መሻሻሎች ይኑር እንጂ በሁሉም ዘረፍ እኝህን የማህበረሰብ ክፍሎች በተገቢው ልክ አካቶና ታሳቢ አድርጎ በመሥራት ረገድ ገና ብዙ የሚቀረን በመሆኑ መሠል ስልጠናዎች ፋይዳቸው የጎላ መሆኑን አስረድተዋል ።
በማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት የተዘጋጀውን ሥልጠና በተመለከተ አቶ መዘገበ መና እንዳሉት ፤ ስልጠናው ተቋማቸው በአካባቢው የልማት እንቅስቃሴዎች ከሚያደረገው ንቁ ተሳትፎና የቁሳቁስ ድጋፍ ባሻገር እንደተቋም የክህሎት ሽግግር ለመፍጠር የወጠነው ውጥን አካል መሆኑን ጠቁመው የሥራ ክፍላቸው የማህበረሰብ አገልግሎቱን ሥራ በተጠናና በተቀናጀ መልኩ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል ።
ዘገባው የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው