የአርባምንጭ ትምህርት ኮሌጅ አካዳሚክ ኮሚሽን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ምክክር አድርጓል ።
በቅርቡ በዳይሬክተርነት የተዋቀሩ የሥራ ክፍሎች እንቅስቃሴን የተመለከተው ቀዳሚ አጀንዳ ሲሆን የማህበረሰብ አገልግሎትን ፤ የ2016 የሥራ ዕቅዶችንና ሌሎች አጀንዳዎችን በማንሳት ተወያይቷል ።
ኮሌጁ የዲግሪ መረሃ ግብር እንደመጀመሩ መረሀግብሩን በሚመጥን መልኩ የአደረጃጀት ለውጥ አድርጓል ።
በዚህም ቀደም ሲል በ5 ስትሪም የተዋቀረውን አደረጃጀት ተጫማሪ የሥራ ክፍሎችን በመጨመር በ11 ደይሬክተሮች በአዲስ መልክ እንዲዋቀር ተደርጓል ።
የአደረጃጀት ለውጡ የኮሌጁን ራዕይ ባጠየቀና ዘመኑን በሚዋጅ መልኩ በሁሉም መመዘኛ ብቁና ተወዳዳሪ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የመገንባት ውጥን አካል ስለመሆኑ በኮሌጁ ዋና ዲን አቶ አያሌው አበራ ተገልጿል ።
ከተፈጠረው የኑሮ ውድነት አንጻር የተማሪዎች ወራዊ የቀለብ ክፍያ ለማሻሻል፤ ለተማሪዎች የዶርምና የህክምና አገልግሎቶችን ለማስጀመር ኮሌጁ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሁሉ በመቀናጀት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ሀላፊው ገልጸዋል ።
ከማህበረሰብ አገልግሎት አንጻር ኮሌጁ ከቁሳዊ ድጋፍ ባሻገር የክህሎት ሽግግር ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ አዲስ የአሰራር ሥርዓተ (platform ) እየዘረጋ መሆኑ በውይይቱ የተጠቀሰ ሲሆን በዚህም ሁሉም መምህራን በማህበረሰብ አገልግሎት የሚሳተፉበትና ኮሌጁ የአጫጭር ስልጠናዎች ማዕከል የሚሆንበት አዲስ የአሰራር ሥርዓት እየዘረጋና ራሱን በቴክኖሎጂ እያደራጀ ስለመሆኑ ተጠቁሟል ።
በመማር ማስተማሩ ሂደትና በጥናትና ምርምሩ ዘረፍ በኮሌጁ እየታዩ ያሉ አበረታች መሻሻሎች በተለያዩ የቦርድ ስብሰባዎች በመልካም ተሞክሮነት መወሰዳቸው ኮሌጁን ትክክለኛ ትራክ ላይ እንዳለ የሚያሳዩ ሲሆን በተለየ ኮሌጁ የትምህርት ጥራት ላይ የጀመረው ዘረፈ ብዙ የሪፎርም ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በውይይቱ ተመላክቷል።
ዘጋባው የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Gefälschte Rolex-Uhren in der Schweiz zu verkaufen, billige replica uhren kaufen im Präsidentenstil mit hoher Qualität zu verkaufen, Rolex-Imitationsuhren online kaufen.